የመቐለ እና ወልዋሎ ጨዋታ የቀን ለውጥ ሊደረግበት ይችላል

ቀጣይ እሁድ በትግራይ ስታዲየም እንዲደረግ መርሐ-ግብር የተያዘለት የመቐለ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ ጨዋታ በአንድ ቀን ተራዝሞ ሰኞ የሚደረግበት ዕድል የሰፋ ነው።

በትግራይ ስታዲየም ዙርያ በሚካሄደው ሃይማኖታዊ በዓል ምክንያት የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ባለሜዳው ቡድን መቐለ 70 እንደርታ ከአንድ ሳምንት በፊት ለአወዳዳሪው አካል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ጨዋታውም ሰኞ የሚካሄድበት ዕድል የሰፋ እንደሆነ ከአወዳዳሪው አካል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በስታድየም አከባቢ ባለው ሃይማኖታዊ በዓል ምክንያት የሰው መጨናነቅ እና የመንገድ መዘጋጋትን ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮችም እንዳያጋጥሙ የቀን ለውጥ የሚደረግበት ይህ ጨዋታ ቀድሞ ቅዳሜ እንዲካሄድ ጥያቄ ቢቀርብም በዛን ቀን ስሑል ሽረ ከአዳማ ከተማ ከሚያደርጉት ጨዋታ ጋር ስለሚደራረብ ነው ጨዋታው ሰኞ እንዲካሄድ የታሰበው።

©ሶከር ኢትዮጵያ