በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ፈረሰኞቹ መካከል ድርድር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፈው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል ድርድር ተደርጓል።

የዘንድሮውን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሁሉንም ውድድሮች በቀጥታ ማስተላለፍ የቻለው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች እንዲያስተላልፍላቸው በቅርቡ ድርድር በማድረግ መግባባት ላይ እየደረሱ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

በሁለቱ መካከል ጨዋታዎቹን በቀጥታ ለማስተላለፍ ድርድሩ እንደተጠናቀቀ እና በፌዴሬሽኑ በኩል የሚጠበቁ አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች እስኪጠናቀቁ ድረስ እየተጠበቀ እንደሆነ ሰምተናል። ድርድሩ ፍሬ አፍርቶ የሚጠናቀቅ ከሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበርን ስፖንሰር እያደረጉ የሚገኙት የሜድሮክ ግሩፕ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ ክለቡን በፋይናስ ረገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ