ለ20 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከ20 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኞች ያዘጋጀውን የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላለፉት ሦስት ቀናት ማከናወኑን በድረ-ገፁ ገልጿል።

በ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉ 17 ክለብ አሰልጣኞችን ያሳተፈውና ታኅሳስ 14 የተጀመረው ይህ ስልጠና በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ቴክኒክ እና ልማት ኮሚቴ ተዘጋጅቶ በሀገር ውስጥ ኢንስትራክተሮች ተከናውኖ ዛሬ ተጠናቋል። በቅርቡ እንደሚጀምር ለሚጠበቀው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግም ጥሩ መዘጋጃ ይሆናል ተብሎለታል።

ከ20 ዓመት ፕሪምር ሊግ ጋር በተያያዘ ፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴ አማካኝነት የተጫዋቾች የእድሜ ምርመራ በጳውሎስ ሆስፒታል እየተካሄደ ይገኛል። የመጀመርያ ዕይታ እና MRI ምርመራን ያካተተው ይህ ምርመራ በሳምንቱ መጀመርያ የተጀመረ ሲሆን ነገ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ