ቅድመ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

የአምስተኛው ሳምንት ማሳረጊያ የሆነው ተጠባቂው የትግራይ ክልል ደርቢን እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

በሳምንቱ ከሚደረጉት ጨዋታዎች ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል በሁለት ዓመታት የሊጉ ቆይታቸው የቅርብ ተፎካካሪዎች የሆኑትን ቡድኖች የሚያገናኘው ይህ ጨዋታ የሚጠቀስ ነው።

በሊጉ ጅማሬ ላይ ወጥ አቋም ማሳየት ተስኗቸው ባላፈው ሳምንት ወሳኝ የሜዳ ውጪ ጨዋታ ያሸነፉት ምዓም አናብስት በርካታ ቋሚ ተጫዋቾቻቸው በጉዳት ከጉዳት መልስ ሲያገኙ በሦስተኛው የሜዳ ክፍል ያላቸው የሰመረ ጥምረትም የቡድኑ ጠንካራ ጎን ነው።

ባለፉት ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት የተጫዋቾች የቦታ ሽግሽግ አድርገው በተመደው በረጃጅም ኳሶች እና በሁለቱም አጥቂዎች መሰረት ያደረገ አጨዋወት የመረጡት መቐለዎች በዚ ወሳኝ ጨዋታ ወሳኝ የአማካይ ተጫዋቾቻቸውን ከጉዳት መልስ ማግኘታቸውን ተከትሎ የሚያጠቁበት መንገድ ላይ ብዙ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ከጉዳት የተመለሰው ዮናስ ገረመው ወደ መጀመርያ አሰላለፉ የሚገባ ከሆነ የአማካይ ክፍሉ ላይ የቅርፅ ለውጥ ይጠበቃል።

በአንፃሩ ባለፉት ጨዋታዎች የተጋጣሚ ረጃጅም ኳሶች ለመከላከል ሲቸገር የታየው ቡድኑ የተጋጣሚን ዋነኛ የማጥቂያ መንገድን ለመግታት በተከላካይ ክፍሉ ላይ መጠነኛ የቅርጽ ለውጥ ማድረጉ አይቀሬ ይመስላል።

ምዓም አናብስት በነገው ጨዋታ ዳንኤል ደምሱ እና ዮናስ ገረመው ከጉዳት ሲመለሱላቸው በረጅም ጉዳት የሚገኘው አምበሉ ሚካኤል
አሁንም ወደ ጨዋታው አይደርስም።

መልካም አጀማመር በማድረግ የሚገኙት እና ሊጉን በአስር ነጥብ በመምራት የሚገኙት ወልዋሎዎች ጥሩ አጀማመራቸው ለማስቀጠል አልመው ወደ ጨዋታው ይገባሉ።

የተጫዋቾች ሚና በመቀያየር ጠጣር እና በመልሶ ማጥቃት የሚያጠቃ ቡድን ይዘው ወደ ውድድር የቀረቡት ወልዋሎዎች ቋሚ ተሰላፊዎቻቸውን ከጉዳት መልስ ማግኘታቸውን ተከትሎ በርካታ ለውጦች ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ሳምንት ካርሎስ ዳምጠው እና ፍቃዱ ደነቀን በጉዳት በማጣታቸው ገናናው ረጋሳ በተከላካይ መስመር ላይ ከአይናለም ኃይለ ጋር ያጣመሩት ቢጫ ለባሾቹ ሁለቱም ቋሚ ተሰላፊዎቻቸው ከጉዳት በመመለሳቸው ለውጦች ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከጅማ አባጅፋር ጋር አቻ በተያዩበት ጨዋታ የተለመደው የመስመር አጨዋወታቸው በተሳካ ሁኔታ መተግበር ያልቻሉት ወልዋሎዎች በተጠቀሰው አጨዋወት ላይ ማሻሻያዎች ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል።

ቢጫ ለባሾቹ አቼምፖንግ አሞስን በጉዳት ሲያጡ ካርሎስ ዳምጠው እና ፍቃዱ ደነቀ ከጉዳት ተመልሰውላቸዋል።

የእርስ በርስ ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪምየር ሊጉ አራት ጊዜ ተገናኝተው ሁለት ጊዜ አቻ ሲለያዩ መቐለ አንድ፣ ወልዋሎ አንድ ጊዜ ድል አስመዝግበዋል። ቀይ ለባሾቹ 3፣ ቢጫ ለባሾቹ ደግሞ 2 ጎል አስቆጥረዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ

መቐለ 70 እንደርታ (4-4-2)

ፊሊፕ ኦቮኖ

ሥዩም ተስፋዬ – አሌክስ ተሰማ – ላውረንስ ኤድዋርድ – አንተነህ ገ/ክርስቶስ

አሸናፊ ሀፍቱ – አሚን ነስሩ – ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ_ያሬድ ከበደ

አማኑኤል ገ/ሚካኤል – ኦኪኪ ኦፎላቢ

ወልዋሎ (4-1-4-1)

ዓብዱልዓዚዝ ኬይታ

ምስጋናው ወ/ዮሐንስ – ፍቃዱ ደነቀ- ዓይናለም ኃይለ – ሳሙኤል ዮሐንስ

ገናናው ረጋሳ

ሰመረ ሀፍታይ – ካርሎስ ዳምጠው – ራምኬል ሎክ – ኢታሙና ኬይሙኔ

ጁንያስ ናንጂቡ


© ሶከር ኢትዮጵያ