አራተኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላልወሰነ ጊዜ እንደሚቋርጥ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
የፌዴሬሽኑ መረጃ ይህንን ይመስላል፡-
የኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድኖች በቀጣይ ከዩጋንዳ እና ከቡሩንዲ አቻዎቻቸው ባለባቸው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ዛሬ ታህሳስ 21 ባካሄደው ሳምንታዊ ስብሰባ አሳወቀ፡፡
ውድድሩ ለመራዘሙ ምክንያት በመሆን የቀረበው በርካታ ተጫዋቾች ለብሄራዊ ቡድኑ በየእድሜ ደረጃው በመመረጣቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ታህሳስ 18/2012ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድር ጨዋታዎች ለ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ሴት ብሄራዊ ቡድን 6ተጫዋቾችን ካስመረጠው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቡድን በስተቀር ውድድሮቹ በተያዘላቸው የጨዋታ ፕሮግራም መሰረት እንዲካሄዱ ተወስኗል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ