ሀዲያ ሆሳዕና አንድ ተጫዋች የውሃ ሽታ ሆኖበታል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዲስ አዳጊው ሀዲያ ሆሳዕናን የተቀላቀለው መሐመድ ናስር ላለፉት ሁለት ሳምንታት ከቡድኑ የልምምድና የጨዋታ ወቅቶች ባለመገኘቱ ክለቡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አውጥቶበታል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲዳማ ቡና ሲያገለግል የቆየውና በዘንድሮ ውድድር ዘመን ነብሮቹን የተቀላቀለው መሐመድ ናስር በሦስተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቡድኑ ወደ ድሬዳዋ አቅንቶ ድሬዳዋን በገጠመበትና የ1ለ0 ሽንፈት ባስተናገደበት ጨዋታ በመጀመሪያ ተሰላፊነት መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን ከጨዋታው መልስ ግን የውሃ ሽታ ሆኗል።

ላለፉት ሁለት ሳምንታት ደብዛው የጠፋው ተጫዋቹ በሥራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለማውጣት መገደዳቸውንና ሁኔታውን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ማሳወቃቸውን ለማወቅ ተችሏል ።


© ሶከር ኢትዮጵያ