ድሬዳዋ ከተማ ለአምስት ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ደካማ የውድድር ዓመት ጅማሮ እያደረገ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ አምስት የቡድኑ ተጫዋቾችን የቃል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡

ቡድኑ በዓመቱ አንድ ድል ብቻ አስመዝግቦ በሰንጠረዡ ከወገብ በታች የሚገኝ ሲሆን ለውጤት መጥፋቱ የተወሰኑ ቋሚ ተሰላፊዎቹን በጉዳት ከማጣቱ ባሻገር የተጫዋቾች አቋም መውረድ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ የሚጠቀስ ሲሆን አምስት ተጫዋቾችም አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። አማካዮቹ ቢኒያም ጥዑመልሳን እና ከድር እዮብ፣ የመስመር አጥቂው ፈርሀን ሰዒድ እና ኮንጓዊው አማካይ ፍሬድ ሙሸንዲ እንዲሁም ዘንድሮ ክለቡን የተቀላቀለው ናይጄሪያዊው አጥቂ ባጅዋ አደሰገንም ማስጠንቀቂያው የደረሳቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡

በተያያዘ ዜና ቡድኑ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ በረከት ሳሙኤል እና ሳሙኤል ዘሪሁን ጉዳት ማስተናገዳቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ለማገገም 15 ቀናት ከሜዳ እንደሚርቁ ክለቡ ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ