በ2017 የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ግብፅ ጋር ተደልድላለች

ማዳካስካር ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣርያ ድልድሉ አርብ ሲወጣ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ተደልድላለች፡፡

ግብፅ ከ ኢትዮጵያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በሁለተኛው ዙር ሲሆን ደቡብ አፍሪካ፣ አንጎላ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ኮትዲቯር፣ ጋቦን፣ ጊኒ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒጀር፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ እና ዛምቢያ ሌሎች በሁለተኛው ዙር ማጣሪያውን የሚቀላቀሉ ናቸው፡፡ ናይጄሪያ ከ ኒጀር፣ ሴኔጋል ከ ቱኒዚያ እና ግብፅ ከኢትዮጵያ ካሃኑ የታወቁ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ናቸው፡፡

የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ከሐምሌ 29 – ነሐሴ 1 ባሉት ቀናት ውስጥ ሲደረግ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከነሐሴ 13 – 15 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ውድድሩን በ2015 ያዘጋጀችው ኒጀር ስትሆን ማሊ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡

 

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች

ጋና ከ ላይቤሪያ

ሊቢያ ከ አልጀሪያ

ሞሪታኒያ ከ ሞሮኮ

ቤኒን ከ ሴራ ሊዮን

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ ቻድ

ሱዳን ከ ጅቡቲ

ማላዊ ከ ኬኒያ

ታንዛኒያ ከ ሲሸልስ

ናምቢያ ከ ቦትስዋና

ሌሶቶ ከ ሞሪሸስ

ኮሞሮስ ከ ዚምባቡዌ

ያጋሩ