ኢትዮጵያ በ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሶማልያን ትገጥማለች 

ባሳለፍነው አርብ የሩዋንዳ መዲና በሆነቸው ኪጋሊ የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች እና ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋነጫ የማጣሪያ ድልድል ወጥቷል፡፡

በ2017 ዛምቢያ ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ኢትዮጵያ ጎረቤት ሶማልያን በመጀመሪያ ዙር ትገጥማለች፡፡

በመጀመርያው የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሶማልያን ከመጋቢት 23-25 ውስጥ ስታስተናግድ የመልሱ ጨዋታ ሚያዝያ 14-16 ባሉት ቀናት ይደረጋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ቤኒን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን፣ ኮንጎ ብራዛቪል ፣ ኮትዲቫር፣ ጋቦን፣ ጋና፣ ግብፅ፣ ሌሴቶ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ሞሮኮ፣ ማላዊ፣ ናይጄሪያ እና ሴኔጋል ማጣሪያው ላይ ከሁለተኛ ዙር ጀምሮ የሚሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ እና ሶማልያ አሸናፊ በሁለተኛው ዙር ጋናን ይገጥማል፡፡

ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና በሚል ስም የሚታወቀው ውድድሩ ናይጄሪያ በ2015 ሻምፒዮን ሆናለች፡፡

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች

ኢትዮጵያ ከ ሶማልያ

ቱኒዚያ ከ ኒጀር

ላይቤሪያ ከ ጊኒ

ሴራ ሊዮን ከ ጋምቢያ

አልጄሪያ ከ ሞሪታኒያ

ሱዳን ከ ኬኒያ

ብሩንዲ ከ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

ሩዋንዳ ከ ዩጋንዳ

አንጎላ ከ ቻድ

ሞዛምቢክ ከ ሞሪሸስ

ስዋዚላንድ ከ ናምቢያ

ዚምባቡዌ ከ ቦትስዋና

ያጋሩ