የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 5-0 ሀዲያ ሆሳዕና

በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ሀዲያ ሆሳዕናን በሰፊ የግብ ልዩነት ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።


👉 “ቡድናችን ገና የምንፈልገው ደረጃ አልደረስሰም” ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለ ጨዋታው

” ቡድናችን ገና በምንፈልገው ደረጃ አልደረስሰም፤ የሆነ ብልጭ ድርግም የሚል ነገር አለ። አንዳንዴ ጨዋታን እንቆጣጠራለን ከዛም ይጠፋል፤ ከዛ መልሶ እንደገና ይቆጣጠሩታል። ከዛ የተነሳ ጨዋታው አንድ ወጥ ይዘት አልነበረውም። ከዚህ የተነሳ ገና የሚቀሩን ነገሮች አሉ።”

ስለተጫዋቹ እንቅስቃሴ

” እንዳለ ለእኔ ጥሩ ነው፤ ጎል ከማግባቱ ውጭ እንቅስቃሴውን ያስተካክላል፤ ፊት ላይ ሆኖ ተጫዋቾች ይጠብቃል፤ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል የማድረግ ባህሪ አለው። ሌላው አንዳንድ የሚሰሩት ስህተት እንግዲህ ከደጋፊው ጫና ውስጥ ያለመውጣት ነገር ነው። አንዳንድ የተሳቱትን ኳሶችን ስንመለከት የደጋፊውን ጫና ካለመቋቋም የመነጨ የሚሰሩ ስህተቶች ናቸው። በተጨማሪም አንዳንድ በዕይታ የሰራቸው ስህተቶች አሉ፤ በሂደት እያረምን ለመሄድ እንሰራለን።”


👉 “በሰራናቸው ስህተቶችና ተጫዋቾችቻችን በጫና ውስጥ ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ ተበልጠን ተሸንፈናል” ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለ ጨዋታው

“ከተከታታይ ሽንፈቶች ብንመጣም ለዛሬው ጨዋታ ጥሩ ዝግጅት አድርገን ነበር። የተሻለ ዝግጅት አድርገናል ብለን ብናስብም ኢትዮጵያ ቡና ከጥሩ ጨዋታ ጋር በተለይ በመጀመሪያ አጋማሽ በሰራናቸው ስህተቶችና ተጫዋቾችቻችን በጫና ውስጥ ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ ተበልጠን ልንሸነፍ ችለናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ