የሊጉ መሪ ወልዋሎ እና ሀዋሳ ከተማን ያገናኘው ጨዋታ ባዶ ለባዶ መጠናቀቁ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።
👉 “ማሸነፍ ይገባን ነበር፤ ግን አልሆነም” ዮሐንስ ሳህሌ
ስለ ጨዋታው
በተጎዱ ተጫዋቾች ምክንያት የአማራጭ ማነስ አጋጥሞናል። ይህም አንዳንድ ያገኘናቸው ዕድሎች እንዳንጠቀም አድርጎናል። አዳዲስ ተጫዋቾች በማስገባታችን የልምድ ማነስ ችግር ፈጥሮብናል። ያገኘናቸው ዕድሎችም መጠቀም አልቻልንም። ግብ ጠባቅያችን ጥሩ ነበር። የመጀመርያ ጨዋታው ነው፤ በዚ ከቀጠለ ኬታንም ማስቀመጥ የሚችልበት ደረጃ ደርሷል። ሌላው ግን ማሸነፍ ይገባን ነበር፤ ግን አልሆነም። የሶስቱ ተጫዋቾች መውጣት ስልታችንን እንድንቀይር አድርጎናል።
👉 “ሁለታችንም ያገኘነውን አጋጣሚ አልተጠቀምንም” አዲሴ ካሣ (ሀዋሳ ከተማ)
ስለ ጨዋታው
ጨዋታው ጥሩ ነበር። ሁለታችንም የማግባት አጋጣሚዎች አግኝተን ነበር ሁለታችን አልተጠቀምንበትም። ከሁለት ሽንፈት በኃላ ስለመጣን፤ ጨዋታውም ከሜዳችን ውጭ ስለሆነ በጥንቃቄ ነው የተጫወትነው።
ስለ መጀመርያው አጋማሽ ቅያሪ
ያልታሰበ ቅያሪ ነው። ጉዳት ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።
ስለ ተጋጣሚያቸው የመስመር አጨዋወት
ከመስመር የሚላኩ ኳሶች አደገኛ ናቸው። አፈትልኮ የሚወጣ አጥቂ መጠበቅ ከባድ ነው።
በተመሳሳይ ከመስመር ሶስት የሚሆኑ ሙከራዎች ሞክረውናል። እኛም ከዕረፍት በፊት ሁለት ያለቀላቸው ኳሶች ስተናል። ሁለታችንም ያገኘነውን አጋጣሚ አልተጠቀምንም።
ስለ ሊግ ጉዟቸው እና የቡድኑ እቅድ
ቡድናችን በወጣቶች የተገነባ ነው። የደሞዝ ነገር ፍርክስክሳችን አውጥቶናል። ብዙ ተጫዋቾች ለቀናል፤ አስራ አራት የሚደርሱ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው። ቀስ እያልን ወደ ጥሩ ብቃት እንመጣለን። በተለይም በሁለተኛው ዙር ጥሩ እንሆናለን ብዬ ጠብቃለው።
© ሶከር ኢትዮጵያ