ሀዲያ ሆሳዕና ከሴራሊዮናዊው ተጫዋቹ ጋር ተለያየ

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም ያደገው ሀዲያ ሆሳዕና በክረምቱ ካስፈረመው ሴራሊዮናዊ አጥቂ ሙሳ ካማራ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በሊጉ የደረጃ ሠረንጠረዥ ግርጌ ላይ የተቀመጠው ሀድያ ሆሳዕና ሙሳ ካማራን ያስፈረመው በክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በሊጉ ጅማሮ በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ እምብዛም ግልጋሎት አልሰጠም። ከስድስቱ የሊግ ጨዋታዎችም በሦስቱ ላይ (98 ደቂቃዎች) ላይ ብቻ ተጫውቶ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

የሴራሊዮን ኢንተርናሽናል እና ዌስት ኢንዲስ የቀድሞ አጥቂ ሙሳ ካማራ ሀዲያ ሆሳዕናን መልቀቁን ተከትሎ በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ማሊ ክለብ እንደሚያመራ ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ