የአሰጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 2 – 0 አዳማ ከተማ

መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው አዳማ ከተማን ካሸነፈ በኃላ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሰጡት ሀሳብ እንደሚከተለው አቅርበናል። የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አስተያየት ግን ማግኘት አልቻንም።

👉 “እንደነበረን ብልጫ እና እንደፈጠርነው ዕድል አላስቆጠርንም” ገብረመድህን ኃይሌ (መቐለ)

ስለ ጨዋታው

ጨዋታውን ስላሸነፍን ጥሩ ነው። ሆኖም እንደነበረን ብልጫ እና እንደሞከርነው ግብ አላስቆጠርንም። ያለቀላቸው ዕድሎችን አምክነናል። በመጀመርያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥርም በሙከራም የተሻልን ነበርን። በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ አጨራረስ ላይ ጥሩ ነበርን። ሆኖም በአጋማሹ እነሱም ተጭነው ተጭውተዋል። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ጥሩ ጨዋታ ነበር። አጨዋወታችን ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ገብተን ግብ ማስቆጠር ላይ መሰረት ያደረገ ነበር። አጨራረስ ላይ አሁንም ብዙ ነገር ይቀረናል።

ስለ ማጥቃቱ ጥምረት

ኦኪኪ ግብ ከማስቆጠር ውጭ እንቅስቃሴው ጥሩ ነገር አለው። አንዳንድ ጊዜ ግብ ማስቆጠር በመፈለግ ነገሮች አይሳኩልህም። በአጠቃይ እንቅስቃሴው ሲታይ ግን ጥሩ ነው። መናበባቸው ጥሩ ነው በሂደት ጥሩ የማጥቃት ጥምረት ይኖረናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ