ጋናዊው የስሑል ሽረ ተከላካይ በጉዳት ከሜዳ ይርቃል

ባሳለፍነው ሳምንት የጎን አጥንት ጉዳት የደረሰበት አዳም ማሳላቺ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

በጥሩ ወቅታዊ ብቃት የሚገኘው የመሐል ተከላካዩ ከሰበታ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ደርሶበት በዕረፍት ሰዓት ወደ ሆስፒታል ያመራ ሲሆን ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ባይረጋገጥም ጉዳቱ ከበድ ያለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በሁለት የተለያዩ ሳምንታት በሶከር ኢትዮጵያ የሳምንቱ ምርጥ 11 የተካተተው ማሳላቺ ዛሬ አመሻሽ የመጨረሻ ህክምና የሚደረግለት ሲሆን ወላይታ ድቻን ለመግጠው ወደ ሶዶ እንደማያመራ ተረጋግጧል። ለምን ያህል ጊዜ እንደሚርቅም ዛሬ ይታወቃል ተብሏል።

በ2010 ለሳምንታት ከመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው አዳም ማሳላቺ ከዚ በፊት ለሊብያው አል ኢግታሚ ትሪፖሊ፣ ለኢኳቶርያል ጊኒው ክለብ ፉትሮ ኪንግስ እና ለሀገሩ ክለብ ስታደ ፉትስ ተጫውቶ አሳልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ