የቱኒዚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያውያን ዳኞች ተጠባቂውን የሊግ ጨዋታ እንዲመሩለት ጠቀየ

የቱኒዚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኤስፔራንስ ደ ቱኒስ እና ኤቷል ዱ ሳህል መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዲመሩት ለኢትዮጵያ አቻው በደብዳቤ መጠየቁን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በድረ-ገፁ እንደጠቆመው ከአፍሪካ ምርጥ ዳኞች ተርታ የሚሰለፈው በዓምላክ ተሰማ ይህንን የቱኒዚያ ሊግ መርሐ ግብር እንዲመራ የተጠየቀ ሲሆን አብረውት የሚመሩት ረዳቶቹ ደግሞ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ መሠረት እንዲላክለት በደብዳቤ ጠይቋል። ፌዴሬሽኑ ከጥያቄው ባሻገር ስለሰጠው ምላሽ ግን ያለው ነገር የለም።

የቱኒዚያዎቹ ኃያላን ክለቦች ቱኒዚያ ፕሮፌሽናል ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀራቸው 2ኛ (ኤስፔራንስ) እና 5ኛ (ዱ ሳህል) የተቀመጡ ሲሆን በመጪው ረቡዕ ተጠባቂውን ጨዋታ የሚያከናውኑ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ