ባምላክ ተሰማ ነገ የሚደረገውን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ይመራል

በግብፁ ዛማሌክ እና በዛምቢያው ዜዝኮ ዩናይትድ መካከል የሚደረገውን የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቹ እንደሚመሩት ታውቋል።

ነገ አመሻሽ በግብፁ አልሠላም ስታዲየም የሚደረገውን ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ባምላክ ተሰማ በዋና፣ ተመስገን ሳሙኤል በረዳት እንዲሁም ለሚ ንጉሴ በአራተኛ ዳኝነት ከግብፁ መሐመድ ኢብራሂም ጋር በመሆን እንደሚመሩ የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል (ካፍ) አስታውቋል።

በምድብ አንድ የሚገኙት ዛማሌክ እና ዜዝኮ እስካሁን 3 የምድብ ጨዋታዎችን አከናውነው አራት እና ሁለት ነጥቦችን (በቅደም ተከተላቸው) በመሰብሰብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ