በፕሪምየር ሊጉ አንድ ጨዋታ ላይ የቀን ለውጥ ተደረገበት

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ15ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ቅዳሜ ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኞ ተሸጋግሯል፡፡

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት የአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይደረጋሉ፡፡ ከእነኚህ ጨዋታ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም የፊታችን ቅዳሜ በ9:00 ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኞ 10:00 ተዛዋውሯል፡፡ የቀን ለውጡ ያስፈለገውም ቅዳሜ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የድምፀዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት በመኖሩ የፀጥታ አካላት በበቂ ሀኔታ ላይኖሩ ስለሚችሉ እንዲሁም ከተማዋ ላይ በአንድ ቀን ሌላ ፕሮግራም መኖር ስለሌለበት በሚል ነው ተብሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ