ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ

የ2012 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት እና ዓመታዊ ስብሰባ ትላንት በፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት ተከናውኗል።

በቦታው የተገኙት የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው በMRI ምርመራ እና ሌሎች በቅድሚያ መከናወን የሚገባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው የውድድሩ መጀመርያ እንደዘገየ ተናግዋል።

ከውይይት እና ገለፃዎች በኋላ በተከናወነው ድልድል 18 ቡድኖች በሁለት ምድቦች የተከፈሉ ሲሆን ሱሉልታ ከተማ ውድድሩን የተቀላቀለ አዲስ ክለብ ሆኗል።

የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-

ምድብ ሀ

ሲዳማ ቡና
ሀዋሳ ከተማ
ወላይታ ድቻ
መከላከያ
ጥሩነሽ ዲባባ ወ/ስ/አካዳሚ
ኢትዮጵያ ወ/ሰ/ አካዳሚ
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድሬዳዋ ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና

ምድብ ለ

አሰላ ኅብረት
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ፋሲል ከነማ
ወልቂጤ ከተማ
አዳማ ከተማ
ኢትዮጵያ መድን
ሀላባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ
ሱሉልታ ከተማ

* ውድድሩ መቼ እንደሚጀምር አልተገለፀም።

* ሙሉውን መርሐ ግብር የውድድር ቀናት ሲገለፁ እናደርሳለን።

* ዘገባውን ያጠናቀርነው ከፌዴሬሽኑ ድረገፅ ባገኘነው መረጃ መሠረት ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ