ገብረክርስቶስ ቢራራ – የመጀመርያ ተሰናባች አሰልጣኝ?

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ዛሬ በሜዳው ከተሸነፈ በኋላ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ስለ ቆይታቸው አስተያየት ሰጥተዋል።

ድቻ ዛሬ በሜዳው በስሑል ሽረ 2-0 መሸነፉን ተከትሎ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የክለቡ ቦርድ በሥራቸው ለመቀጠል በሁለት ጨዋታዎች ላይ ውጤታቸውን እንዲያስተካከሉ የሰጠው እድል ባለመሳካቱ ከዚህ በኋላ በኃላፊነታቸው የመቀጠላቸው ነገር እንዳበቃለት ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ክለቡን የተረከቡት በዚህ ዓመት ሲሆን ቡድኑ በሊጉ ከስምንት ጨዋታ አንድ ብቻ አሸንፎ በሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛል። አሰልጣኙ የስንብት ውሳኔ ከተላለፈም ሊጉ ከተጀመረ ወዲህ የመጀመርያው ይሆናል።

በአሰልጣኙ ቆይታ ዙርያ ከክለቡ የምናገኘውን መረጃ በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ