የአሰልጣኞች አስተያየት| ወልዋሎ 0-1 ሀዲያ ሆሳዕና

ሀድያ ሆሳዕና ከሜዳው ውጪ ወልዋሎን 1-0 ካሸነፈበት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።

👉 “እንደ ነበረው እንቅስቃሴ ውጤቱ ይገባናል” ኢዘዲን ዓብደላ (የሀዲያ ሆሳዕና ምክትል አሰልጣኝ)

ስለ ጨዋታው

እንደጠበቅነው ነው የተጫወትነው። ተጫዋቾቻችን በምንፈልገው ልክ ተንቀሳቅሰዋል። እንደነበረው እንቅስቃሴ ውጤቱ ይገባናል። ውጤቱ ጨዋታውን ይገልፀዋል። የፈጠርናቸው ዕድሎች ብንጠቀም ከዚ በላይ ማስቆጠር እንችል ነበር።

ስለ ቡድኑ

እስካሁን ባደረግናቸው ጨዋታዎች ከዕለት ዕለት እያሻሻልን የተሻለ ነገር እያደረግን ነው። ቡድናችንም እየተሻሻለ ወደምንፈልገው ደረጃ እየሄደ ነው።

👉 “ኳስ ጨዋታ አንዳንዴ እንዲህ ነው” ዮሐንስ ሳህሌ (ወልዋሎ)

ስለ ጨዋታው

ኳስ ጨዋታ አንዳንዴ እንዲ ነው። ዕድል አገኙ፤ ተጠቀሙ። በምንም መንገድ አገቡ ቀደሙን ማግገም አልቻልንም ጨዋታውንም አሸነፉን።

ስለ ቡድኑ የሁለተኛ አጋማሽ እንቅስቃሴ

እንቅስቃሴ ዋጋ የለውም ነጥቡን እስካላገኘህ ድረስ። አንዳንድ ጊዜ ከተቀደምክ የማትመለስበት ጊዜ አለ።

ስለ ቡድኑ ክፍተቶች

ክፍተት አይደለም፤ አንዳንድ ግዜ መዘናጋት አለ።
አዳዲስ ተጫዋቾች ታስገባለህ እነሱ ሲገቡም ይሳሳታሉ ይህ የኳስ ፀባይ ነው። ብዙ ግዜ ነበረን፤ ያገቡት መጀመርያ አጋማሽ ነበር። መመለስ እንችል ነበር።


© ሶከር ኢትዮጵያ