የአቡበከር ናስር የጉዳት መጠን ዛሬ ይታወቃል

በትላንትናው ዕለት ጉዳት ያስተናገደው አቡበከር ናስር የጉዳት ሁኔታ ዛሬ ይታወቃል።

ቡናማዎቹ ትናንት በስምንተኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጎንደር ላይ በፋሲል ከነማ 2-1 ሽንፈት ባስተናገዱበት ጨዋታ ገና በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ከዐፄዎቹ ግብ ጠባቂ ሳማኬ ጋር የተጋጨው አቡበከር ናስርን ጉዳት በማስተናገዱ በአላዛር ሽመልስ ተቀይሮ ለመውጣት መገደዱ ይታወቃል።

የጉዳቱን መጠን እና ዓይነት ምን እንደሆነ ጠይቀን እንዳረጋገጥነው የቁርጭምጭሚቱ ጉዳት እንደሆነ እና ቡድኑ ዛሬ ከጎንደር አዲስ አበባ እንደገባ የኤክስሬ ህክምና ተደርጎለት የጉዳቱ መጠን ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚታወቅ ሲሆን በአጠቃላይ የአቡበከር በቀጣይ ጨዋታዎች የመድረስ አለመድረሱ ጉዳይ አመሻሽ ላይ ቁርጡ እንደሚታወቅ ሰምተናል።

በአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ቡድን ከፍተኛ ሚና ያለው አቡበከር በቀጣይ ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት ከሜዳ የሚርቅ ከሆነ በቡናማዎቹ የማጥቃት ሚዛን ላይ ክፍተት እንዳይፈጥር ተሰግቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ