አቡበከር ናስር ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል

በስምንተኛው ሳምንት ጨዋታ ጎንደር ላይ ጉዳት ያስተናገደው የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ታውቋል።

ከፋሲል ከነማ ጋር ትናንት በነበረው ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ከግብ ጠባቂው ሳማኬ ጋር የተጋጨው አቡበከር ናስር ዛሬ የኤክስሬይ ህክምና ምርመራ አድርጓል። ምንም እንኳ ጉዳቱ ለክፉ የማይሰጥ ቢሆንም ለሁለት አልያም ለሦስት ሳምንታት በቂ እረፍት እንዲያደርግ ተነግሮታል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና በሜዳው እና ከወልዋሎ ጋር ከሜዳው ውጭ የሚደረገው ጨዋታ እንደሚያመልጠው ሲረጋገጥ በ11ኛው ሳምንት ለሚደረገው ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ