ወጣቱ አጥቂ በጉዳት ሀዋሳን አያገለግልም

የሀዋሳ ከተማው የፊት መስመር ተጫዋች መስፍን ታፈሰ በጉዳት ለሀዋሳ ግልጋሎት አይሰጥም፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መልካም እንቅስቃሴን ከሚያደርጉ ወጣት ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሰው የሀዋሳ ከተማው አጥቂ በሰባተኛው ሳምንት በሜዳው ሰው-ሰራሽ ሜዳ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ባጠናቀቁበት ጨዋታ ላይ በ60ኛው ደቂቃ በጡንቻ መሸማቀቅ ምክንያት በብርሀኑ በቀለ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በስምንተኛው ሳምንትም ቡድኑ ወደ አዳማ ተጉዞ 1ለ1 ሲለያይ በጉዳት ያልተሰለፈ ሲሆን አሁንም በቂ የማገገሚያ ጊዜ እስኪያገኝ በቀጣይ የሊጉ ሁለት ጨዋታዎች ላይ የማይሰለፍ ይሆናል፡፡

ዐምና መጋቢት ወር ላይ ከተስፋ ቡድኑ ካደገ በኃላ በሊጉ ክስተት መሆን የቻለውና በተደጋጋሚ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የደረሰው መስፍን በዚህ ዓመት በሊጉ አንድ ጎል ሲያስቆጥር አንድ ኳስ አመቻችቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ