በኮስታሪካ እና ፓናማ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታውን ቅዳሜ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 18 ተጫዋቾች በመያዝ ወደ ቡሩንዲ አቅንቷል።
በኢትዮጵያ ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ ለቀናት ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል እና ህይወት አረፋይኔ እየተመራ አስቀድሞ ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች ውስጥ የተወሰነ ለውጥ በማድረግ ነው 18 ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው።
ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ካምፓላ በማቅናት ከዩጋንዳ ጋር ከተጫወተው ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የመጀመርያ ተሰላፊ ከነበሩት መካከል ነፃነት ፀጋዬ እና ይመችሽ ዘውዴን ዳግመኛ ከሳምንት በኃላ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦላቸው ወደ ቡሩንዲ ሊያቀኑ ችለዋል።
ወደ ቡሩንዲ ያቀኑ 18 ተጫዋቾች ዝርዝር
ግብጠባቂዎች
ዓባይነሽ ኤርቄሎ፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ
ተከላካዮች
ናርዶስ ጌትነት፣ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ታሪኳ ደባስ፣ ብርቄ አማረ፣ ማህደር ባዬ፣ ነፃነት ፀጋዬ
አማካዮች
እመቤት አዲሱ፣ ገነት ኃይሉ፣ የምስራች ላቀው፣ አረጋሽ ካልሳ፣ ሲሳይ ገ/ዋህድ፣ ይመችሽ ዘውዴ
አጥቂዎች
ዮርዳኖስ ምዑዝ፣ ምርቃት ፈለቀ፣ ረድኤት አስረሳህኝ፣ ሥራ ይርዳው
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ ጋር ቅዳሜ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ