በ9ኛ ሳምንት በሀዋሳ ስታዲየም ከመልካም የሊጉ ጅማሮ ማግስት በውጤት መቀዛቀዝ ውስጥ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች ወልቂጤ ከተማን የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ተከታዩ ዳሰሳችን ተመልክቶታል።
ሁለት ተቃራኒ የሆኑ የጨዋታ አቀራረብ በሚጠቀሙ ሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው ይህ ጨዋታ ለቡድኖቹ ሶስት ነጥቡ ካለው ዋጋ አንፃር ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተሰሎ ይጠበቃል።
የሀዋሳ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) | ||||
አቻ | አቻ | አቻ | ተሸነፈ | ተሸነፈ |
በአሰልጣኝ አዲስ ካሴ የሚመራውና ለመከላከል አደረጃጀት የበዛ ትኩረት የሚሰጠው ቡድኑ በ8 ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በጨዋታ በአማካይ ከአንድ ያነሰ ግብ በማስቆጠር በሊጉ ከተጋጣሚው ወልቂጤና ወላይታ ድቻ ቀጥሎ አነስተኛ ግብን ያስቆጠረ ቡድን እንዲሆን አድርጎታል። ይባስ ብሎ በመስመሮች በኩል የቡድኑን የማጥቃት እንቅስቃሴ የሚመራው መስፍን ታፈሰ ባጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ መራቁ በሳሳው የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ሌላ ሳንካ የፈጠረ አጋጣሚ ሆኗል።
በሀዋሳ ከተማ በኩል ጉዳት ላይ የሚገኙት አጥቂዎቹ እስራኤል እሸቱ እና መስፍን ታፈሰ በጉዳት የነገው ጨዋታ የሚያመልጣቸው ሲሆን በተመሳሳይ ከጉዳት ያገገመው ቸርነት አውሽ ጨዋታው የሚያመልጠው ይሆናል። የአለልኝ አዘነ መኖርም አጠራጣሪ ነው።
የወልቂጤ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) | ||||
ተሸነፈ | ተሸነፈ | አቻ | አሸነፈ | ተሸነፈ |
በአንፃሩ ወልቂጤዎቹ ዘንድሮ ወደ ሊጉ ከተቀላቀሉ ቡድኖች መካከል በወጥነት ጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን በማሳየት ላይ የሚገኙት ሰራተኞቹ እስካሁን በሊጉ 2 ጨዋታዎችን ብቻ ሲያሸንፉ በተቀሩት ጨዋታዎች መልካም የሚባልን አዎንታዊ የጨዋታ አቀራረብን ሜዳ ላይ ቢያስመለክቱም ብኩን የሆነው የቡድኑ የአጥቂ መስመር ቡድን ከጨዋታዎች ሙሉ ሶስት ነጥቦችን ይዞ እንዳይወጣ እየተገዳደረው ይገኛል።
በዚህ ሳምንት ለአራት የቡድኑ ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ የሰጡት ወልቂጤ ከተማዎች መከተል ለሚያስቡት የኳስ ቁጥጥር አጨዋወት በተመቸው የሀዋሳው ሰው ሰራሽ ስታዲየም ለባለሜዳዎቹ እጅግ ፈታኝ ሊሆኑባቸው እንደሚችሉ ይጠበቃል።
በወልቂጤዎች በኩል አዳነ በላይነህ በጉዳት ጨዋታው የሚያመልጠው ሲሆን ተከላካዩ ቶማስ ስምረቱን ጨምሮ አዳነ ግርማንና ፍፁም ተፈሪን ግልጋሎት የሚያገኝ ይሆናል።
እርስ በርስ ግነኙነት
– ጨዋታው ለሁለቱ ቡድኖች በሊጉ የመጀመርያ ግንኙነት ይሆናል።
ግምታዊ አሰላለፍ
ሀዋሳ ከተማ (4-2-3-1)
ቤሊንጋ ኢኖህ
ዳንኤል ደርቤ – ላውረንስ ላርቴ – መሳይ ጳውሎስ – ያኦ ኦሊቨር
ብርሃኑ በቀለ – ተስፋዬ ነጋሽ – ሄኖክ ድልቢ – አክሊሉ ተፈራ
ብሩክ በየነ – ሄኖክ አየለ
ወልቂጤ ከተማ (4-3-3)
ይድነቃቸው ኪዳኔ
ይበልጣል ሽባባው – ዐወል መሀመድ – ዳግም ንጉሴ – አቤነዘር ኦቴ
አብዱልከሪም ወርቁ – አልሳሪ አልመህዲ – በረከት ጥጋቡ
ሄኖክ አወቀ – ጃኮ አራፋት – ጫላ ተሺታ
© ሶከር ኢትዮጵያ