2022 ዓለም ዋንጫ| የኢትዮጵያ የምድብ ማጣርያ ተጋጣሚዎች ተለይተዋል

ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ድልድል የተደረገ ዛሬ ይፋ ሲሆን ዋልያዎቹ በምድብ ‘ G’ ተደልድለዋል።

የማጣርያው ምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በካይሮ ናይል ሪትዝ ሆቴል ይፋ የሆነ ሲሆን ማጣርያውም በርካታ ተጠባቂ ጨዋታዎች አካቷል።

በቅድመ ማጣርያው ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚል ህግ ወደ ምድብ ድልድሉ የገባችው ኢትዮጵያም በምድብ ‘G’ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ተደልድላለች።

ቀድሞ በወጣው መርሀግብር የማጣርያው ጨዋታዎች በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ አራት እስከ ሰባት ሴፕተምበር የሚጀመሩ ሲሆን ሁለተኛው ጨዋታም በቀናት ልዩነት ውስጥ ከስምንት እስከ አስር ሴፕተምበር የሚደረጉ ይሆናል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ