የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዝውውር የሚከፈትበት ቀን ታውቋል

የ2012 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን አጋማሽ የተጫዋቾች ዝውውር የሚከፈትበት ቀን ተለይቶ ታውቋል።

የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የአንደኛው ዙር እንደተጠናቀቀ ከነበረባቸው ክፍተት በመነሳት ራሳቸውን ለማጠናከር ከሚጠቀሙበት መንገድ አንዱ የሆነው የሁለተኛው አጋማሽ የዝውውር እንቅስቃሴ ከየካቲት 16-መጋቢት 16 ድረስ ለአንድ ወር እንደሚቆይ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የዝውውር ሂደቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን ዝውውሩ ውሰትን እንደሚጨምር ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ