የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ተራዘመ

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በ18 ቡድኖች መካከል በዚህ ሳምንት ሊጀምር የታሰበው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተራዝሟል።

ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚጀምር ለክለበቹ መረጃ የደረሳቸው ቢሆንም ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለአንድ ሳምንት እንደተራዘመ ሰምተናል። ውድድሩ ለአንድ ሳምንት ይራዘም እንጂ አሁንም ቢሆን በተባለበት ጊዜ የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል።

በሌላ ዜና በምድብ ሀ ተደልድሎ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ራሱን ከውድድሩ በማግለል ወደ በአዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዮን ለመወዳደር እንዳሰበ መስማታችንን ተከትሎ የፌዴሬሽኑ ህዝብ ግንኙነት አቶ ባህሩ ጠይቀን “እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆን፤ የተጫዋቾችን ውል እያሰራ መሆኑን እና በውድድሩ እንደሚሳተፍ ነው የምናውቀው” ብለዋል”።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ አመራሮች የሚሰጡትን ምላሽ እንዳገኘን የምናቀርብ ይሆናል።

ፎቶ፡ በዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓቱ ወቅት የተነሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ