የአዲስ አበባ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

ከዓምናው የተሳታፊ ቁጥሩ የጨመረው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር የምድብ ድልድል ሥነ ሥርዓት ትናንት ተካሄደ።

ከ2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥር መካሄድ የጀመረው ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር ዘንድሮ ቁጥሩ ከ10 ወደ 15 ቡድኖች ከፍ በማለት ይካሄዳል። ትናንት በአራት ኪሎ በወጣቶች ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውድድሩ አዘጋጅ አካል እና ተሳታፊ ክለቦች በተገኙበት በተሻሻሉ የውድድሩ ደንቦች እና ተዛማጅ በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት ከተደረገ በኃላ ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሁለት ዙር ጨዋታ በማድረግ ከየምድባቸው ከአንድ እስከ ሁለት የወጡ ቡድኖች በጥሎ ማለፍ በሚያደርጉት ጨዋታ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይ ይሆናል።

ዓምና ተሳታፊ ከነበሩ ቡድኖች ሠላም እና የኢ/ወ/ስ አካዳሚ በዚህ ውድድር የማይሳተፉ ሲሆን
ዲ ኤፍ ቲ፣ ሰውነት ቢሻው፣ ከለላ፣ ጉ ቻናል፣ ፍቅር በአንድነት፣ ቤተል ድሪም እና ጌታቸው ቀጨኔ ውድድሩን የተቀላቀሉ አዳዲስ ቡድኖች ናቸው።

በ2011 በኤሌክትሪክ አሸናፊነት የተጠናቀቀው ይህ ውድድር የዘንድሮው በቀጣይ ሳምንት ጥር 23 እና 24 እንደሚጀምር ታውቋል።

ምድብ ሀ

ቅዱስ ጊዮርጊስ
አዳማ ከተማ
ቤተል ድሪም
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ኢትዮጵያ ቡና
ከለላ
ጉ ቻናል
ፍቅር በአንድነት

ምድብ ለ

ጌታቸው ቀጨኔ
ኢትዮጵያ መድን
መከላከያ
ሀሌታ
አፍሮ ፅዮን
ዲ ኤፍ ቲ
ሰውነት ቢሻው


© ሶከር ኢትዮጵያ