በዘጠነኛው ሳምንት የቅዳሜ መርሐ ግብር አካል የሆው የሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታን እንደሚከተለው ተመልክተነዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም እያደረጋቸውሚገኙ ጨዋታዎችን በተከታታይ እያሸነፈ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከነገው ጨዋታ ሙሉ ሦስት ነጥብ ማግኘት ደረጃውን ለማሻሻል ወሳኝ ነው።
የሰበታ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) | ||||
ተሸነፈ | አሸነፈ | ተሸነፈ | አሸነፈ | አቻ |
የውበቱ አባተ ቡድን አሰልጣኙ በድሕረ ጨዋታ አስተያየት እንደሚገልፁት አጨዋወቱን ከተጋጣሚያቸው ባህርይ አንፃር የሚቃኝ በመሆኑ በነገው ጨዋታ ኳስን በተጋጣሚ የሜዳ ክፍል ተቆጣጥሮ የጎል እድሎችን ለመፍጠር እንደሚጥር ይጠበቃል። ቡድኑ ጎሎችን ከተለያየ የአጨዋወት አማራጭ ለማግኘት የሚጥር መሆኑ ጠንካራ ጎኑ ሲሆን በነገው ጨዋታ የማጥቃት ወቅት ከጀርባቸው ጥለውት የሚሄዱትን ክፍተት በፈጣን የመልሶ ማጥቃት አደጋ ሊፈጥሩ የሚችሉት የሀዋሳ ተጫዋቾችን የሚከላከሉበት መላ መዘየድ ይጠበቅባቸዋል።
ሰበታዎች ዳዊት እስጢፋኖስ፣ በኃይሉ አሰፋ፣ አስቻለው ግርማ እንዲሁም እስከ ዓመቱ መጨረሻ በጉዳት አይደርስም የተባለው ተከላካዩ ሳቪዮ ካቩጎ ከጨዋታው ውጪ ሆነዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) | ||||
አሸነፈ | አቻ | አቻ | አቻ | ተሸነፈ |
ከተከታታይ ድል አልባ ጉዞ በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሀዋሳ ከተማ ባለፈው ሳምንት ያሳካውን ድል ለመድገም አልሞ ወደ ሜዳ ይገባል።
ቡድኑ ለመተንበይ አስቸጋሪ የሆነ አጨዋወት የሚከተል ቢሆንም ከሜዳ ውጪ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያዘወትረው ጥንቃቄ የተሞላበት አቀራረብ በነገው ጨዋታም የሚጠበቅ ነው። ቡድኑ ከተጋጣሚው አንፃር ኳስ ቁጥጥር ላይ ዝንባሌ የሌለው በመሆኑ ኳሱን ለሰበታ በመስጠት ወደራሳቸው የሜዳ ክፍል በማመዘን በቀጥተኛ ኳሶች አደጋ ለመፍጠር ይጥራሉ ተብሎ ይገመታል። እየተሻሻለ የመጣው የአማካይ ክፍል እና በአጥቂዎቹ ጉዳት ምክንያት የቡድኑን የጎል ማስቆጠር ጫና የተሸከመው ብሩክ በየነ ለሀዋሳ ውጤታማነት ቁልፍ ሚና እንደሚኖራቸውም ይጠበቃል።
በሀይቆቹ በኩል ከጉዳት ያገገመው መስፍን ታፈሰ መግባቱ አጠራጣሪ ሲሆን እስራኤል እሸቱ አይኖርም።
እርስ በርስ ግንኘነት
በሊጉ ከዚህ ቀደም ለስድስት ጊዜያት ተገናኝተው ሰበታ 3 በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን ሀዋሳ 1 ድል አስመዝግቧል። በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል።
– በስድስቱ ጨዋታዎች ሰበታ 5 ሲያስቆጥር ሀዋሳ 4 አስቆጥሯል።
ግምታዊ አሰላለፍ
ሰበታ ከተማ (4-3-3)
ዳንኤል አጃይ
ጌቱ ኃይለማርያም – አዲስ ተስፋዬ – ወንድይፍራው ጌታሁን – ኃይለሚካኤል አደፍርስ
ታደለ መንገሻ – ደሳለኝ ደባሽ – መስዑድ መሐመድ
ሲይላ ዓሊ – ፍፁም ገ/ማርያም – ባኑ ዲያዋራ
ሀዋሳ ከተማ (4-4-2)
ቤሊንጋ ኢኖህ
ዳንኤል ደርቤ – ላውረንስ ላርቴ – መሳይ ጳውሎስ – ያኦ ኦሊቨር
ሄኖክ ድልቢ – ዘላለም ኢሳይያስ – ተስፋዬ መላኩ – ብርሀኑ በቀለ
ሄኖክ አየለ – ብሩክ በየነ
© ሶከር ኢትዮጵያ