ምንተስኖት አሎ በቱርክ የሙከራ ዕድል አግኝቷል

የስሑል ሽረ ግብ ጠባቂ ምንተስኖት አሎ የውጭ የሙከራ ዕድል አገኘ።

በዚ ዓመት መጀመርያ ወደ ስሑል ሽረ አምርቶ ከቡድኑ ጋር ጥሩ የውድድር ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ምንተስኖት አሎ በቱርክ ዋናው ሊግ በሚወዳደረው አንታልያስፖር እና በሁለተኛው የሊግ እርከን በሚገኘው ደሚርስፖር በተባሉ ሁለት ክለቦች ነው የሙከራ ዕድሉን ያገኘው።

ባለፉት አራት ጨዋታዎች ግቡን ያላስደፈረው ይህ ግብ ጠባቂ በዚህ ሰዓት የጉዞ ሂደቱን ለማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ያመራ ሲሆን በነገው ዕለት ውስጥ ወደ ስፍራው ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ለሰበታ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ መጫወት የቻለው ግብ ጠባቂው ባለፈው ዓመት ለዋናው ብሄራዊ ቡድን መጫወት ጀምሮ ብሄራዊ ቡድኑ አይቮሪኮስትን ባሸነፈበት ጨዋታ ተቀይሮ ገብቶ መጫወቱም ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ