ምዓም አናብስት ወሳኙ ተጫዋቻቸውን በጉዳት አጥተዋል

የመቐለ 70 እንደርታው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል በልምምድ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከዛ ጨዋታ ውጪ ሆኗል።

የባለፈው ውድድር ዓመት የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ አማኑኤል በዚህ ዓመትም 70 እንደርታዎቹ የሊጉን ዋንጫ ለሁለተኛ ግዜ ለማንሳት በሚያደርጉት ጉዞ ስድስት ግቦች በማስቆጠር የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን ያስመሰከረ ሲሆን በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ጋር ወደ ሶዶ አላመራም። ሆኖም የተጫዋቹ የጉዳት ሁኔታ ቀላል እንደሆነ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በፊት ለጉዳት እምብዛም ተጋላጭ ያልነበረው ፈጣኑ አጥቂ ከሳምንታት በፊት ለክለቡ ሀምሳኛው ግቡን ማስቆጠሩ ሲታወስ በአጠቃላይ ዘንድሮ በ10 ጎሎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ