የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ዳኞችን በሚመለከት መልዕክት አስተላለፈ

ከተመሠረተበት ቅርብ ጊዜነት አንፃር በርካታ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን የውድድር ዳኞችን አስመልክቶ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገባ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ላይ መድረሱን በደብዳቤው የገለፀው ማኅበሩ በዚህ መልኩ መልዕክቱን አስተላልፏል

“በነዚህ ዘጠኝ የውድደር ጊዜያት ማህበሩ ከስፖርት ቤተሰቡና ከእግርኳሱ ሙያተኞች በዳኝነቱ ላይ የሚታዩ ችግሮች እያሳሰባቸው መምጣቱን ይገልፃሉ። አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ለጋዜጠኞች ከጨዋታ መጠናቅ በኃላ በሰጠው መግለጫ ላይ እንደተናገረው “ዳኞቻችን ከተለያዩ ስሌቶች ውስጥ መውጣት አለባቸው ብዬ አስባለው የትም ቦታ ጨዋታውን ሲመሩ የጨዋታውን ህግ ላይ ማተኮር አለባቸው” የሚለውን ሀሳብ ማኅበራችን የሚጋራው ነው። ይህን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ በመውሰድ እግርኳሳችን ችግር ውስጥ እንዳይገባ ሠላም እንዳይደፈርስ ከዚሁ ክትትል በማድረግ መፍትሔዎች እንዲያፈላልግ” የ?ብሏል።

እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች ወይም መልዕክቶች ከክለቦች ከመቅረብ ባለፈ በማኅበራት ደረጃ ያልተለመደ ሲሆን ይህን መልዕክት ያስተላለፈበት መንገድ አስገራሚ ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ