ቅድመ ዳሰሳ | ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

በሊጉ አስረኛ ሳምንት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል የወልቂጤ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታን የዳሰሳችን ማሳረጊያ አድርገነዋል።

ከወጣ ገባ አቋም በኋላ ባለፉት ተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዶ የሠንጠረዡ ግርጌ ላይ የተቀመጠው ወልቂጤ ከተማ ከሽንፈት ስነ-ልቦና ለመውጣት እና ከግርጌው ለመላቀቅ የነገውን ጨዋታ ማሸነፍ ላይ ተመስርቶ ወደ ሜዳ ይገባል።

የወልቂጤ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ)
ተሸነፈ ተሸነፈ ተሸነፈ አቻ አሸነፈ

 

የውህደት እና ሥልነት ችግር በስፋት የሚስተዋልበት ወልቂጤ ከተማ በሊጉ ዝቅተኛ ግብ (3) ያስቆጠረ ቡድን መሆኑ በፊት መስመሩ ላይ ያለውን ድክመት የሚያሳይ ነው። በነገው ጨዋታ የሚገጥመው ድሬዳዋ ከተማ እንዳለፉት የሜዳ ውጪ ጨዋታዎቹ ሁሉ በራሱ ሜዳ ተገድቦ በተደራጀ መከላከል የሚገባ ከሆነ ለወልቂጤ ነገሮችን ሊያከብድ ይችላል።

ኳስ ለመቆጣጠር የማይቸገረው ቡድኑ በነገው ጨዋታም ከተጋጣሚው ባህርይ ጋር ተዳምሮ የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱን እንደሚይዙ የሚጠበቁ ቢሆንም በአደጋ ክልል የሚኖራቸው የቅብብል ስኬት እና እድሎችን በአግባቡ መጠቀም ውጤት ይዘው ለመውጣት ማተኮር የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው።

ቡድኑ በነገው ጨዋታ በጉዳትም ሆነ በቅጣት የሚያጣው ተጫዋች የለም።

የድሬዳዋ ከተማ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ)
አሸነፈ ተሸነፈ ተሸነፈ አሸነፈ አቻ

ከአጀማመሩ አንፃር መጥፎ የማይባል ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ በነገው ጨዋታ ድል በማስመዝገብ ከወራጅ ቀጠናው ለመራቅ ወደ ሜዳ ይገባል።
ለወትሮው ከሜዳው ውጪ ደካማ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት ሁለት የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች አራት ጎሎች ማስቆጠሩ እና አንድ ድል ማስመዝገቡ ስለመሻሻሉ ምስክር ነው ማለት ይቻላል። ቀስ በቀስ ተጫዋቾች ከጉዳት እየተመለሱ ቡድኑን እያሟላ መገኘቱም በነገው ጨዋታ ቀላል ግምት እንዳይሰጠው ያደርጋል።

ብርቱካናማዎቹ በነገው ጨዋታ ለጥንቃቄ ቅድሚያ በመስጠት እና ኳሱን ለተጋጣሚያቸው በመተው የመከላከል አቀራረብን ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል። ከመከላከል ባሻገርም በሚገኙ ክፍተቶች የጎል እድሎችን እነረደሚፈጥሩ ይጠበቃል። በተለይ ጥሩ አቀቀም ላይ የሚገኘው ሙህዲን ሙሳ፣ ያሬድ ታደሰ እና ጠንካራው ሪችሞንድ አዶንጎ በሽግግሮች ላይ የሚኖራቸው ውጤታማነት ለቡድኑ ወሳኝ ነው። የቡድኑ አንፃራዊ የቆመ ኳስ ስኬትም ሌላው ጠንካራ ጎኑ ነው።

በድሬዳዋ በኩል ጨዋታ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ከራቀው ረመዳን ናስር ውጪ ተጨማሪ የጉዳት ዜና የለም። በአንፃሩ ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ከጉዳት አገግሟል።

እርስ በርስ ግንኙነት

– ሁለቱ ቡድኖች ነገ ለመጀመርያ ጊዜ በሊጉ ይገናኛሉ።

ግምታዊ አሰላለፍ

ወልቂጤ ከተማ (4-2-3-1)

ሶሆሆ ሜንሳህ

ይበልጣል ሽባባው – ዐወል መሀመድ
ዳግም ንጉሴ – አቤኔዘር ኦቴ

ኤፍሬም ዘካሪያስ – በረከት ጥጋቡ

አባይነህ ፊኖ – አብዱልከሪም ወርቁ ጫላ ተሺታ

ጃኮ አራፋት

ድሬዳዋ ከተማ (4-2-3-1)

ሳምሶን አሰፋ

ፍሬዘር ካሣ – ያሬድ ዘውድነህ – አማረ በቀለ – ያሲን ጀማል

ፍሬድ ሙሸንዲ – ዋለልኝ ገብሬ

ያሬድ ታደሰ – ኤልያስ ማሞ – ሙህዲን ሙሳ

ሪችሞንድ ኦዶንጎ


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ