ሎዛ አበራ በዛሬ ምሽት ጨዋታ ግቦች አስቆጥራለች

ሎዛ አበራ ሁለት ግቦች ባስቆጠረችበት ጨዋታ ቢርኪርካራዎች የቅርብ ተፎካካሪያቸውን ረተዋል።

የማልታ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ከዓለማቀፍ ጨዋታዎች ዕረፍት መልስ ሲጀመር ሎዛ ያለችበት ቢርኪርካራ ስዌቂን 5-0 አሸንፏል። በጨዋታው ሎዛ አበራ በስልሳ አምስተኛው እና በሰማንያኛው ደቂቃ ላይ ሁለት ጎሎች ስታስቆጥር የተቀሩትን ግቦች ኢስታር አኑ (2) እና ራንያ ጉስቲ አስቆጥረዋል።

የዛሬ ውጤት ተከትሎ ቢርኪርካራዎች ከተከታያቸው ስዌቂ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ ሲያደርጉ ሎዛ አበራም የሊግ ጎል መጠኗን ሀያ ስድስት አድርሳለች።

ሊጉ በቀጣይ ሳምንትም ቢቀጥልም የሎዛ አበራ ቡድን ቢርኪርካራ ግን ከአስራ ሶስት ቀናት በኃላ በሜዳው ሞስታን ያስተናግዳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ