የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ባህር ዳር ከተማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህር ዳር ከተማን 1-0 ከረታበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።


👉 “በጨዋታው የተሻለው ቡድን አሸንፏል” ሰርዳን ዝቪጅኖቭ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

“ጨዋታው ለእኛ በጣም ከባድ ነበር። ከመሪው መቐለ ላለመራቅ የግድ ሦስት ነጥብ ያስፈልገን ስለነበር ከፍተኛ ጫና ውስጥ ነበርን። ጨዋታውን በመጀመሪያው አጋማሽ እንደመቆጣጠራችን የፈጠርናቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም አለመቻላችን ለተጋጣሚያችን በጨዋታው እንዲቆዩ እድል ሰጥናቸው ነበር። ይህም ጨዋታውን አክብዶብናል። በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ መንቀሳቀስ ችለን ግብ አስቆጥረናል፤ በአጠቃላይ በጨዋታው የተሻለው ቡድን አሸንፏል።”

👉 “ውጤቱ ጨዋታውን ይገልፀዋል ብዬ አላስብም” ፋሲል ተካልኝ (ባህርዳር ከተማ)

ስለ ጨዋታው

“በመጀመሪያ ተጋጣሚያችን ሦስት ነጥብ ስላሳኩ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ተጫዋቾቼ ከዚህ ሜዳ ነጥብ ይዘው ለመውጣት የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል፤ እነሱ ሊያጠቁ የሚችሉባቸውን ቀዳዳዎች ዘግተን እኛ የግብ እድሎችን ለመፍጠር ሞክረናል። ነገርግን ያገኘናቸውን እድሎች መጠቀም አለመቻላችን የኃላ ኃላ ዋጋ አስከፍሎናል። እንደአጠቃላይ ውጤቱ ጨዋታውን ይገልፀዋል ብዬ አላስብም።”

ስለ ሳሙኤል ተስፋዬ ተጋላጭነትና ቀይ ካርድ

“ሳሙኤል ጥሩ እየተጫወተ ነበር። እንደ ወጣት ተጫዋች ጥሩ ተንቀሳቅሷል. በሒደት ስህተቶቹን ያርማል። በእሱ ስፍራ ከተሰለፈው ተጫዋች ያነሰ ተንቀሳቅሷል ብዬ አልወስድም። መጨረሻ ላይ የራሱን ውሳኔ እንደ ተጫዋች ወስኗል። ይህ ደግሞ የሚያጋጥም ነው።”


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ