ኢትዮጵያ ቡና በሸገር ደርቢ ወሳኙን ተጫዋች እንደማያገኝ ተረጋግጧል

የሸገር ደርቢ ጨዋታ ላይ የመድረስ አለመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ሆኖ የቆየው የኢትዮጵያ ቡና ወሳኝ አጥቂ በነገው ጨዋታ ላይ አለመድረሱ እርግጥ ሆኗል።

በስምንተኛው ሳምንት ጎንደር ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ወጣቱ አጥቂ አቡበከር ናስር ምንም እንኳ ከጉዳቱ አገግሞ ልምምድ የጀመረ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ለነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ዝግጁ ባለመሆኑ እንደማይጫወት ታውቋል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ የአቡበከርን አገልግሎት የማያገኝ በመሆኑ የአጥቂ መስመሩን እንዳለ ደባልቄ እና ሀብታሙ ታደሰ ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ