አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ላይ ወልቂጤ ባለሜዳው ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 ከረታበት ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ በነበረው ችግር ምክንያት የአሰልጣኞች አስተያየት ያልበረ በመሆኑ በስልክ የወልቂጤን አሰልጣኝ አስተያየት ስናገኝ የሀዲያ ሆሳዕናን ማግኘት ባለመቻላችን አላካተትንም።
👉 “ድላችንን አስጠብቀን ለመቀጠል ነበር ወደዚህ የመጣነው” ድግአረግ ይግዛው
ስለ ጨዋታው
ጨዋታው ጥሩ ነበር፤ ጥሩ ፉክክር ታይቶበታል። ሆሳዕናዎች ከሽንፈት እንደመምጣታቸው እኛ ደሞ ድላችንን አስጠብቀን ለመቀጠል ነበር ወደዚህ የመጣነው። ሜዳው ከምናውቀው ውጭ ነበር፤ በጣም ተጉድቷል። በዚህ ሜዳ ኳስን ይዞ መጫወት ከባድ እንደነበር በማወቃችን የጨዋታ አቀራረባችንን በመለወጥ ውጤተማ ሆነናል። ተጋጣሚያችን ሀዲያ ሆሳዕና እጅግ ጠንካራ ነበር። ልጆቻንን ያለውን ጫና ተቋቋመው ይህን ውጤት አስመዝግበውል።
ስለተፈጠረው ችግር
ጨዋታው ላይ ግቡ ከተቆጠረ በኋላ ድንጋይ ውርወራ ነበር። በዚህም ረዳቴ ተመቷል። እኛም ወደሜዳ ገብተን ነው የተርፍነው። መጨረሻ ላይ የተፈጠረው ነገር ደግሞ በጣም አሳዛኝ ነው። ወደ አላስፈላጊ ድርጊት ነበር ያመራው። የልዩ ሀይሉ ባይቆጣጠረው እንዲሁም የቡድኑ አመራሮች እርዳታቸው ባይደርጉ ኖሩ ችግር ይባባስ ነበር። በዚሁ አጋጣሚ የሆሳዕና ወጌሻ የሆነው አቶ ቢንያም ላደረገው መልካም ትብብር በኔም በቡድኔም እንዲሁ በወልቂጤ ደጋፊ ስም አመስግናለው።
© ሶከር ኢትዮጵያ