የወልዋሎው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የዲሲፕሊን ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
በ9ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ወልዋሎ ወደ ባህር ዳር ተጉዞ 3-2 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከሳምንታት በፊት ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የሥነ-ምግባር ግድፈት አሳይተዋል በሚል አምስት ጨዋታ እና ስምንት ሺህ ብር ተቀጥተዋል።
ብዙ ክስተት ባስተናገደው ጨዋታ ላይ ወልዋሎ የማሸነፍያዋ ጎል በተቆጠረበት እና ዳኛው ጨዋታውን በመሩበት መንገድ ላይ ቅሬታውን ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ሦስተኛው ጎል ሲቆጠር ባቀረቡት ቅሬታም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ጨተታው ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል።
ቅጣት የተጣለባቸው ዮሐንስ ሳህሌ በአሁኑ ሰዓት ቡድናቸው ሲዳማ ቡናን እየገጠመ የሚገኘውና 1-0 እየተመራ የሚገኘው ቡድናቸውን ለመምራት በስታድየም ያልተገኙ ሲሆን ቅጣቱም እስከ አስራ አምስተኛው ሳምንት የሚዘልቅ ይሆናል።
አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በመቐለ 70 እንደርታ በሚሰሩበት ወቅትም በተመሳሳይ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ቅጣት ተላልፎባቸው አምስት ጨዋታ ቡድናቸውን ሳይመሩ መቅረታቸው ይታወሳል።
© ሶከር ኢትዮጵያ