ያሬድ ዘውድነህ የሙከራ ዕድል አግኝቷል

የድሬዳዋ ከተማው ተከላካይ ያሬድ ዘውድነህ የውጭ ሀገር የሙከራ ዕድል አግኝቶ ወደ መቆዶንያ በቅርቡ ያቀናል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በውጭ ሀገራት በሚገኙ ክለቦች የሙከራ እድል ማግኘታቸው እየተሰማ ባለበት በአሁኑ ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ ያሬድ ዘውድነህ በመቄዶንያ ሀገር የሚገኘው ሲሌክስ የሙከራ ዕድል አግኝቶ በቅርቡ እንደሚጓዝ ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኢትዮጵያ የሚገኘው ኤጀንቱ ይህን ዕድል እንዳመቻቸለት እና ወደ መቆዶንያ ለመጓዝ ህጋዊ ክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ፍቃድ እየተጠባበቀ እንደሆነ የገለፀው ያሬድ ክለቡ የሙከራ ዕድሉን እንዲጠቀም ፍቃድ እንደሰጠውና በቅርቡ ወደ ሥፍራው እንደሚያቀና ተናግሯል።

የአሁኑን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች ለድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ለአዳማ ከተማ፣ ለዳሽን ቢራ፣ ወልዲያ እና ጅማ አባ ጅፋር የተጫወተው ያሬድ ዘውድነህ በቀጣይ ከጉዞው ጋር የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ