የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 5-0 ወልዋሎ

በአስራ አንደኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲዳማ ቡና በሜዳው ወልዋሎን 5ለ0 ከረታ በኋላ የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ አስተያየታቸውን ሲሰጡ የወልዋሎው ረዳት አሰልጣኝ ኪዳኔ ሀፍተይ ጥሩ ስሜት ላይ እንዳልሆኑ በመግለፅ አስተያየት ባለመስጠታቸው ሳናካትት ቀርተናል።

👉 “በተጫዋቾቼ በጣም ኮርቻለሁ” ዘርዓይ ሙሉ (ሲዳማ ቡና)


ከአራት ድል አልባ ጉዞ በኃላ በርካታ ግቦችን አስቆጥራችሁ አሸንፋችዋል። የዛሬው ጨዋታ በሽንፈቱ ዕልህ የተገኘ ነው ማለት ይቻላል…?

ሁለት ሳምንት ከሜዳ ውጪ ተጫውተን ተሸንፈናል፤ የተሸነፍንበትንም ምክንያት እናውቀዋለን፡፡ በሁለቱም ጨዋታዎች ላይ እንሸነፍ እንጂ ቡድናችን ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ነበር። በተለይ ከፋሲል ጋር ባደረግነው ጨዋታ ቡድናችን ጥሩ ቅርፅ ይዞ ነበር፤ ሆኖም በአጋጣሚ ተሽንፈን መጥተናል፡፡ ወልዋሎ ጠንካራ ቡድን ነው። በተለይ በመከላከሉ ረገድ ጠንካራ ቡድን ስለሆነ በዛ ላይ ደግሞ በሚገባ ተዘጋጅተን ነበር የሰራነው። በዚህም በጎል ነበር የታጀበ በጣም ጥሩ ጨዋታ ነበር፡፡ ጎል ጋር ስንደርስ የአጠቃቀም ችግር ስለነበረብን በአዕምሮ ላይ ነበር ተዘጋጅተን የገባነው፡፡ ደጋፊዎቻችን ሁለቱን ጨዋታ ውጤት አጥተው ታግሰውናል፤ ለዚህም ከልብ ላመሰግን እፈልጋለሁ፡፡

ሲዳማ ቡና ባለፉት ጨዋታዎች ሲያስመዘግብ የነበረው ውጤት ይገባዋል ብለህ ታስባለህ..?

በፍፁም! የሚገርምህ ነገር ዛሬ ለተጫዋቾቼ የነገርኩት ይሄን ነው፡፡ ተጫዋቾቹ የሚሉት እኛ ያለንበት ደረጃ ለኛ አይሆንም የምንቀሳቀስው እና ነጥባችን እኛ አይገልጽም። ያ እንዳልሆነም ዛሬ በሚገባ አሳይዋል፡፡ በተጫዋቾቼ በጣም ኮርቻለሁ፡፡

በመከላከሉ ረገድ የነበረው ክፍተት መሻሻል?

ጥቃቅን ስህተት ነበር ስንሰራ የነበረው። ጊት ገና ወጣት ነው፡፡ ከከፍተኛ ሊግ ነው ነው የመጣው። ገና ልምድ እያገኘ ነው፡፡ ዛሬ ግን ያደረገው እንቅስቃሴ በጣም የሚገርም ነበር። በተደጋጋሚ እዛ ቦታ ነበር ስህተት ስንሰራ የነበረው ጎሎችም ሲቆጠሩብን የነበረው እና እዛ ላይ በመነጋገርም ሆነ በአቋቋም በደንብ ነበር የተማርነው። ያንን ደግሞ ተግባራዊ አድርገውታል፡፡ በዚህም በጣም ደስ ብሎኛል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ