የስሑል ሽረው አሰልጣኝ ሥራ አቁመዋል

የስሑል ሽረው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ከደሞዝ ጋር በተገናኘ ምክንያት ልምምድ ማሰራት አቁመዋል።

በክለቡ ከሐምሌ ጀምሮ ላለፉት ሰባት ወራት ያልተከፈላቸው ደሞዝ እንዳላቸው የተገለፀው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ በዛሬው የቡድኑ ልምምድ ላይ ያልተገኙ ሲሆን ይህ ችግር በቶሎ የማይቀረፍ ከሆነም ከቡድኑ ሊለቁ እንደሚችሉም ሰምተናል። በቀጣይ ቀናት ልምምድ ላይ እንዲሁም ቡድኑ እሁድ መቐለ ላይ ከሀዋሳ ከተማ በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ይገኛሉ አይገኙም የሚለውም ተጠባቂ ጉዳይ ነው። 

አሰልጣኝ ሳምሶን ባለፈው ዓመት አጋማሽ ቡድኑን ተረክበው ከመውረድ ማትረፍ የቻሉ ሲሆን ዘንድሮ ከመጥፎው አጀማመር አገግመው በጥሩ ወቅታዊ አቋም ይገኛሉ። በዚህ ሳምንት ከተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች በኃላ ሽንፈት ማስተናገዳቸውም ይታወሳል። 

ሰለ አሰልጣኙ ሥራ ማቆም እና የክለቡ ሀሳብ እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ ነገሮችን እየተከታተልን እናቀርባለን።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ