ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ : ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኤሌክትሪክ 0-1 ድሬዳዋ ከተማ
-68′ ፍቃዱ ታደሰ

—–*—–

ተጠናቀቀ !!!!
ድሬዳዋ ከተማ በፍቃዱ ታደሰ ብቸኛ ግብ ኤሌክትሪክን ድል አድርጓል፡፡

90+1′ ተቀይሮ የገባው ዮናስ ከግራ የፍፁም ቅጣት ምት ጠርዝ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡ ከግቡ በኋላም ድሬዎች በእንቅስቃሴ እየበለጡ ይገኛሉ፡፡

90′ የመሰረት ማኒ ድሬዳዋ ከተማ የዘንድሮ የውድድር ዘመን የመጀመርያ የአአ ስታድየም ድል ለማስመዝገብ 4 ጭማሪ ደቂቃ ብቻ ቀርቶታል፡፡

*ከዚህ ጨዋታ ቀጥሎ የሚጫወቱት የደደቢት እና ሀዋሳ ከተማ ተጫዋቾች ለማማሟቅ ከመልበሻ ክፍል ወጥተዋል

87′ የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ
ከድር አዩብ ወጥቶ ዮናስ ገረመው ገብቷል፡፡

80′ እንደ ድሬዳዋ ሁሉ ኤሌከትሪክም ከተመሳሳይ ርቀት ቅጣት ምት ቢያገኝም ፒተር ኑዋድኬ በግቡ አግዳሚ ወደ ላይ ሰዷታል፡፡

79′ ድሬዳዋ ከተማዎች በግምት ከ30 ሜትር ርቀት ያገኙትን ቅጣት ምት ዳዊት እስጢፋኖስ መትቶ አሰግድ ይዞበታል፡፡

76′ የተጫዋች ቅያሪ – ኤሌክትሪክ
ማናዬ ፋንቱ በ አብዱልሃኪም ሱልጣን ተቀይሮ ወጥቷል፡፡

* ዳዊት እስጢፋኖስ በጥሩ ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ፍቃዱ ታደሰ ድሬዳዋ ከተማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

68′ ጎል ፍቃዱ ታደሰ !!!!!!!

66′ የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ
በላይ አባይነህ ወጥቶ ፍቃዱ ወርቁ ገብቷል፡፡

* ድሬዳዋ ከተማዎች ወደ ግብ ለመድረስ ባይቸገሩም የአጥቂዎቹ ስል አለመሆን ግብ እንዳያስቆጥሩ አድርጓቸዋል፡፡

59′ የተጫዋች ቅያሪ – ኤሌክትሪክ
ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ ሀብታሙ መንገሻ ገብቷል፡፡
ከቅያሪው በፊት በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ማናዬ ፋንቱ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

56′ የተጫዋች ቅያሪ – ኤሌክትሪክ
ብሩክ አየለ በአሳልፈው መኮንን ተቀይሮ ገብቷል፡፡

56′ ይሁን እንዳሻው በግሩም ሁኔታ ያሻገረውን ኳስ ፍቃዱ ወርቁ ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ቢገናኝም ወደ ውጪ ሰዷታል፡፡

*ለአንድ አመት የታገደው የኤሌክትሪኩ አዲስ ነጋሽ በስታድየም ተገኝቶ የቡድኑን ጨዋታ እየተመለከተ ይገኛል፡፡

50′ የኤሌክትሪኩ ግብ ጠባቂ አሰግድ አክሊሉ እየተፈተነ ይገኛል፡፡ በተደጋጋሚ ኳስ በአግባቡ መቆጣጠር ሲቸገር ተስተውሏል፡፡

48′ አክሌስያስ ግርማ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍቃዱ ታደሰ ሳይደርስበት ቀርቷል፡፡ ግብ ሊሆን የሚችል ጥሩ አጋጣሚ ነበር

47′ ማናዬ ፋንቱ በአፍንጫው ላይ በደረሰበት ጉዳት የህክምና እርዳታ እየተደረለት ይገኛል፡፡

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ፡፡ ኤሌክትሪክ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡

*******

እረፍት ፡ የመጀመርያው አጋማሽ በተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ታጅቦ 0-0 ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ሰአት ተጠናቆ አራተኛ ዳኛው 1 ደቂቃ ጨምረዋል

44′ በላይ አባይነህ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

39′ ፒተር ኑዋድኬ ከርቀት ወደ ግብ የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

35′ ጨዋታው ከተጀመረ ግማሽ ሰአት ተሻግሯል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ በኳስ ቁጥጥር እና ጎል ሙከራዎች ከባለሜዳው ተሽሏል፡፡

27′ ፍቃዱ ታደሰ የሞከራት ኳስ የግቡን ሚ ገጭታ ስትመለስ አክሌሲያስ ግርማ አግኝቷት በድጋሚ ቢሞርም አሰግድ አክሊሉ ግብ ከመሆን አድኗታል፡፡

26′ አክሌሲያስ ግርማ ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ የነበረ በመሆኑ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡

20′ ፒተር ኑዋዲኬ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍፁም ገብረማርያም በግንባሩ ገጭቶ የድሬዳዋ ጎል አግዳሚ መልሶበታል፡፡

12′ ጨዋታው 12 ደቂቃዎች ተጉዟል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች በመሃል ሜዳ የተገደበ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ ፡ ኤሌክትሪክ 0-0 ድሬዳዋ ከተማ

———-
የኤሌክትሪክ አሰላለፍ

አሰግድ አክሊሉ

አወት ገ/ሚካኤል – በረከት ተሰማ – ሲሴይ ሃሰን – ተስፋዬ መላኩ

ማናዬ ፋንቱ – አሸናፊ ሽብሩ – በሃይሉ ተሻገር – አሳልፈው መኮንን

ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ

– – – – – – –

የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ

ሳምሶን አሰፋ

ሄኖክ አዱኛ – ተስፋዬ ዲባባ – ብርሃኑ ሆራ – ፍሬው ብርሃን

ይሁን እንዳሻው – ከድር አዩብ – ዳዊት እስጢፋኖስ

አክሌስያስ ግርማ – ፍቃዱ ታደሰ – በላይ አባይነህ

አሁን ሁለቱም ቡድኖች ማማሟቂያ ከሰሩ በኋላ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *