አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ በነገው ጨዋታ ቡድናቸውን ይመሩ ይሆን?

በትናንትናው ዕለት በደሞዝ ምክንያት ከልምምድ ሜዳ ቀርተው ከቡድኑ ጋር የመቀጠላቸው ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቶ የነበረው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ በነገው ዕለት ቡድናቸው ይመሩ ይሆን የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል።

ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳይ ቅርበት ካላቸው ሰዎች እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ አሰልጣኙ ከክለቡ አመራሮች ጋር ካደረጉት ውይይት በኃላ ነገ በ12ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማን በሚያስተናግዱበት ጨዋታ ጨዋታ ቡድናቸውን ለመምራት እንደወሰኑ ለማወቅ ተችሏል።

አሰልጣኙ በዛሬው ልምምድም ያልተገኙ ሲሆን ክለቡ የተፈጠረውን ችግር ፈትቶ በቀጣይ ቀናት ወደ መደበኛ ሥራቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ