የምንተስኖት አሎ የሙከራ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ እየቀጠለ ነው

ምንተስኖት አሎ በቀጣይ ቀናት በአንታልያ ስፖር ያለውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ደሚርስፖር ያመራል።

ከሳምንታት በፊት በቱርክ ክለቦች አንታልያ ስፖር እና ደሚር ስፖር የሙከራ አድል አግኝቶ ወደ ስፍራው ያቀናው የስሑል ሽረው ምንተስኖት አሎ ጥሩ የሙከራ ግዜ እያሳለፈ እንደሚገኝ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ገልጿል። ላለፉት ሳምንታት በቱርክ ዋናው ሊግ በሚሳተፈው አንታልያስፖር የሙከራ ግዜ እያሳለፈ የሚገኘው ግብ ጠባቂው እያሳየ ያለው ብቃት በግሉም የአሰልጣኞች ቡድኑም ደስተኞች እንደሆኑ ገልፆ ከክለቡ ጋር ያለው የሙከራ ቆይታም በቀጣይ ቀናት እንደሚጠናቀቅ ገልፅዋል።

በቀጣይ ቀናት ወደ ደሚር ስፖር አምርቶ ሌላ የሙከራ ጊዜ የሚያሳልፈው ምንተስኖት አሎ እስካሁን በቱርክ ቆይታው ብዙ ትምህርት እንደወሰደ ጠቅሶ የክለቡ ልምምድ እና የአጠቃላይ የክለቡ ሁኔታ ምቹ እንደሆነ ተናግሯል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ