ቡሩንዲዎች ባህር ዳር ገብተዋል

በፈጠሩት የትኬት አቆራረጥ ስህተት መነሻነት ወደ ድሬዳዋ አምርተው የነበሩት ቡንዲዎች ነገ ጨዋታቸውን ወደሚያደርጉበት ባህር ዳር ከደቂቃዎች በፊት ገብተዋል።

ነገ በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ብሩንዲዎች ዛሬ 5 ሰዓት ወደ ባህር ዳር ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በፈጠሩት የትኬት አቆራረጥ ስህተት ወደ ድሬዳዋ አምርተዋል። ይህንን የቡድኑን ስህተት ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ባከናወኑት ሥራ ቡድኑ ምሽት 4 ሰዓት ጨዋታው ወደሚደረግበት ከተማ (ባህር ዳር) ገብቷል።

በዲላኖ ሆቴል የሚያርፈው ቡድኑ ነገ 10 ሰዓት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድንን ይገጥማል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ