የዓመቱ ፈጣን ጎል ሶዶ ላይ ተቆጠረ

በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሁን ሶዶ ላይ እየተደረገ ባለው የወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ የዓመቱ ፈጣን ጎል ተቆጥሯል።

የወላይታ ድቻው የመስመር ተጫዋች እዮብ ዓለማየሁ የዓመቱን ፈጣን ጎል በ40ኛው ሰከንድ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የእለቱ ዋና ዳኛ እያሱ ፈንቴ ገና ፊንሽካቸውን አሰምተው የድሬዳዋ ተጫዋቾች እንደጀመሩ እድሪስ ሰይድ በፍጥነት ከሪችሞንድ እግር ነጥቆ ወደ ድሬዳዋ የግብ ክልል ከደረሰ በኃላ ብርቱካናማዎቹን የተከላካይ ስህተት ትኩረት ማነስ ተመልክቶ በአየር ላይ ያሻገረለትን ኳስ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ተመልሶ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ እየተጫወተ የሚገኘው እዮብ ዓለማየሁ ከጎሉ ለቆ የወጣው ሳምሶን አሰፋን መረብ ላይ ማሳረፍ ችለል። ሒደቱ የፈጀው 40 ሰከንድም የዓመቱን ፈጣን ግብ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት 35 ደቂቃ የደረሰው ጨዋታው በወላይታ ድቻ 2-0 መሪነት እየቀጠለ ነው።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ