ለበርካታ ዓመታት ፋሲል ከነማን ያገለገለው ሀብታሙ ዘዋለ ራሳቸውን ከፋሲል ከነማ ቡድን መሪነት አንስተዋል።
በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን አስተናግዶ 1-0 ባሸነፈት ጨዋታ ላይ የተወሰኑ የፋሲል ደጋፊዎች በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን ደጋፊዎቹ ተቃውሟቸውን በክለቡ አመራር ኮሚቴዎች እና የቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ ላይም የገለፁ ሲሆን ይህን ተከትሎም ሀብታሙ ዘዋለ በተቃውሞው ደስተኛ እንዳልሆኑ እና ራሳቸውን ከክለቡ እንዳገለሉ ከመሸ ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጫ አግኝታለች ።
ሀብታሙ ዘዋለ ከፋሲል ከነማ ጋር ከታችኛው ሊግ ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት ክለቡን ያገለገለ ሲሆን ክለቡን ፕሪምየር ሊግ ከውሳኔው ጋር በተያያዘ ያሉን ቀጣይ ሁኔታዎች ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ