ድሬዳዋ ከተማ እና አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይ ተለያዩ

ድሬዳዋ ከተማን ከረዳት አሰልጣኝነት ጀምሮ ዘንድሮ ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰቷቸው የነበሩ አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይ ከድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝነታቸው ተነስተዋል፡፡

በሊጉ በወጥነት ውጤት ለማስመዝገብ ከሚቸገሩ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ከአስራ ሁለት ሳምንት ጨዋታዎች አስራ ሶስት ነጥብ ሰብስቦ በአስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይም በክለቡ እየታየ ካለው የውጤት መጥፋት አንፃር ክለቡ ያስቀመጠላቸውን በአግባቡ መተግበር አልቻሉም በማለት ዛሬ ማለዳ ለማሰናበት ተገዷል፡፡ አሰልጣኙ በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ 3 ለ0 ቡድኑ ሲረታ ከመቀመጫ ወንበራቸው ሳይነሱ ሙሉ ዘጠና ደቂቃው የጨረሱ ሲሆን በወቅቱም ሶከር ኢትዮጵያም የአሰልጣኙ ቆይታ አጠራጣሪ መሆኑን በስፍራው ተገኝታ መመልከት ችላ ነበር፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት ከረዳት አሰልጣኝነት በጊዜያዊ አሰልጣኝ ጭምርም በመሆን ዘንድሮ ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ቦታ ላይ ክለቡን ሲመሩ በነበሩት አሰልጣኝ ስምኦን ምትክ ከሴቶች ቡድን አንስቶ ከ2010 ጀምሮ ደግሞ በክለቡ በረዳት አሰልጣኝነት ሲሰራ የነበረው ፍሰሀ ጡዑመልሳን በጊዜያዊነት ክለቡን እስከ አንደኛው ዙር ከመሩ በኃላ አዲስ አሰልጣኝ እንደሚቀጥር ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ