የወልዋሎ አመራር ቦርድ አሰልጣኙን ለማሰናበት ወስኗል

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በዋና አሰልጣኙ ጉዳይ ላይ የተወያየው የወልዋሎ የሥራ አመራር ቦርድ አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ ወሰነ።

በአሰልጣኙ ቆይታ ላይ ዛሬ ጠለቅ ያለ ስብሰባ ያደረገው የክለቡ የቦርድ አመራር አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ ሲወስን ቡድኑ በጊዚያዊነት በአብርሀ ተዓረ እና ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ እየተመራ ጨዋታዎች እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

በተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደው ወደ ወራጅ ቀጠናው የተጠጉት ቢጫ ለባሾቹ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ሰዓት ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በስምምነት መለያየታቸው ሲታወስ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌም በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ከአንድ ዓመት የቡድኑ ቆይታ በኋላ የሚሰናበቱ ይሆናል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በቅጣት ምክንያት ቡድኑን አለመምራታቸው ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ